Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ በደቡብ አፍሪካ አቻቸው 1 ለ 0 ተረቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  ለዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ዉድድር በደቡብ እፍሪካ ኤፍ ኤን ቢ ስታዲየም ዛሬ የተካሄደው የኢትዮጵያ አና የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ በአስተናጋጁ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ በደቡብ አፍሪካ አንድ ለባዶ መሪነት ነው የተጠናቀቀው።

ግቧ የተቆጠረችው ጌታነህ ከበደ በራሱ  ላይ ባስቆጠራት ግብ ነው።

በዚህ ውጤት መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሆኖም የዋለያዎቹ ማጣሪያውን የማለፍ ዕድል በእጅጉ የጠበበ ነው።

በኢትዮጵያ በኩል በሁለኛው አጋማሽ 60ኛው ደቂቃ ላይ ሽመልስ በቀለና አስራት ቶንጆ፥ ሱራፌል ዳኛቸውንና ሱሌይማን ሀሚድን  ቀይረው ወደሜዳ  ገብተዋል።

78ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁ ሁለተኛው የተጨዋች ቅያሬ የተደደረገ ቢሆንም  ዋለያዎቹ የውጤት ለውጥ ማምጣት አልቻሉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ ጨዋታቸውን ከዚሁ ቡድን ጋር  በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተጫውቶ 3 ለ 1 መሸነፉ ይታወሳል።

ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዉድድር ሲሳተፍ የቆየው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር ነበር የተደለደለው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.