Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ነገ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግርኳስ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛ ጨዋታውን ነገ በባህርዳር ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያደርጋል።

ለኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ኢትዮጵያ ከጋና፣ ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ጋር በምድብ ሰባት መደልደሏ ይታወቃል።

በምድብ ድልድሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጋና 1 ለ 0 ሲሸነፍ የዚምባቡዌ አቻውን ደግሞ 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ዋልያዎቹ ነገ ምድቡን በአራት ነጥብ ከሚመራው የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ቡድን ጋር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ፎቶ፡-ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.