Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ የኒጀር አቻቸውን 3ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የኒጀር አቻቸውን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ከኒጀር ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም አካሂዷል።
በጨዋታውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የኒጀር አቻቸውን 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማሸነፊያ ጎሎችንም አማኑኤል ገብረሚካኤል በ14ኛው ደቂቃ፣ መስዑድ መሐመድ በ44ኛው ደቂቃ እንዲሁም ጌታነህ ከበደ በ70ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
ኒጀር ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ኒጀር 1ለ0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ አይቮሪ ኮስት ከማዳጋስካር ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻው ጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
ብሄራዊ ቡድኑ በ2021 ካሜሩን በምታስተናግደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በምድብ 11 ከኮትዲቯር፤ማዳጋስካር እና ኒጀር ጋር ተደልድሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.