Fana: At a Speed of Life!

ውጤታማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግንባታ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን “እናሳካለን ውጤታማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግንባታ ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ ጉባኤ እያካሄደ ነው፡፡

የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፤ ከሃገራዊ ሪፎርሙ ማግስት ጀምሮ ኢንዱስትሪው የሚያገግምበት ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረውለት ዘርፉ የሃገር ገንቢነት ሚናውን ለመወጣት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዘርፉ የተገኙ ስኬቶችን በማሳያነት ያቀረቡ ሲሆን፥ ኢንዱስትሪውን በአግባቡ በመምራት፣ በማስተዳደር እና በመቆጣጠር ስርዓቱ ውስጥ የተለያዩ የህግ ማቀፎች እንዲወጡና እንዲተገበሩ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

በንቅናቄ በመድረኩ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታሳተፊዎች ናቸው፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የ30 ዓመት ፍኖተ ካርታ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ የጥናት ወረቀቶች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.