Fana: At a Speed of Life!

ውጫሌና ውርጌሳ ከተሞች ተቋርጦባቸው የቆየውን ኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ውጫሌና ውርጌሳ ከተሞች በሽብር ቡድኑ ህወሓት ተቋርጦባቸው የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ማግኘታቸውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት በማድረስ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሰባቸው ከተሞች መካከል የሆኑት ውጫሌና ኡርጌሳ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ዳግም አግኝተዋል፡፡

ውጫሌና ውርጌሳ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል እንደገና ማግኘት መቻላቸውን የወልደያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ወ/ሰማያት ተናግረዋል።

ቡድኑ 84 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የደሴ-ወልድያ 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ላይ ጉዳትማድረሱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.