Fana: At a Speed of Life!

ዎዳ ሜታልስ ኩባንያን ወደ ኢንደስትሪ ፓርክ ለማሳደግ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዎዳ ሜታልስን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማሳደግ የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
በስምምነቱ መሰረት÷ ኩባንያው በሰበታ ከተማ አሁን የሚገኝበትን 18 ነጥብ 9 ሔክታር ይዞታ ወደ 100 ሔክታር የማምረቻ ፓርክ እንደሚያሳድግ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢንደስትሪ ፓርኩ በብረት፣ በኢንጂነሪንግ ፣ በኬብል አምራች፣ የአውቶሞቲቭ እና ጎማ አምራች ኢንደስትሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድም ተመላክቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ሕግጋት ባከበረ መልኩ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት እና ለሀገሪቷ ገቢ የሚያስገኙ ምርቶች ላይ አተኩረው እንደሚሰሩም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
ለ17 ሺ 500 ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥረው ፓርኩ፥ ለማስፋፊያው 95 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ዎዳ የብረታ ብረት ማምረቻ አንደስትሪ፥ በ65 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት በማስመዝገብ በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የሚንቀሳቀስ ኩባንያ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.