Fana: At a Speed of Life!

ዐቃቤ ህግ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰማ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 8፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እነ አቶ እስክንድር ነጋ በተጠረጠሩበት የእርስ በርስና የሃይማኖት ግጭት ማስነሳት ወንጀል አራት ምስክሮችን ችሎት አቅርቦ አሰምቷል፡፡

በዚህም 3ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተመዘገቡ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

እነ አቶ እስክንድር በነሃሴ 6 ቀን ጠበቆቻችንን አንፈልግም ብለው ማሰናበታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንዲጠበቅ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ ያቆመላቸውና በዛሬው ዕለት ምስክርን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን እነ አቶ እስክንድር ግን ዛሬም የቆመላቸውን ተከላካይ ጠበቃ አንፈልግም ሲሉ አሰናብተዋል፡፡

ተከላካይ ጠበቃው ተጠርጣሪወቹን ለማማከር ብሞክርም አንፈልግም ጠበቃ የማቆም አቅም ስለሌለን አይደለም ፤ ፍርድ ቤቱም ይህን ሰምቶ ያሰናብተኝ ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አሰናብቶታል፡፡

ዐቃቤ ህግ ያቀረባቸው አራት ምስክሮች ቃላቸውን የሰጡ ቢሆንም አቶ እስክንድር ነጋ በምስክሮቹ ላይ መስቀለኛ ጥያቄ ካለዎት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ “ብዙ ጥያቄ ቢኖረኝም ምንም አይነት መስቀለኛ ጥያቄ ማቅረብ አልፈልግም” ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ቀሪ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለነሃሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.