Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ85 ሚሊየን መብለጡ ተገለጸ፡፡

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ሚሊየን 519 ሺህ በላይ ሲሆን፤ ከ1 ሚሊየን 850 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

አሜሪካ ከ21 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከ360 ሺህ በላይ ዜጎቿ ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እንዲሁም ፈረንሳይ ዜጎቻቸው በቫይረሱ በመያዝ ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ተቀምጠዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ቱኒዚያ እና ኢትዮጵያ ደግሞ ከአፍሪካ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በአንጻሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሚሊየን 485 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.