Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አልፏል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 1 ሚሊየን 16 ሺህ 401 መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

በቫይረሱ ሳቢያ 53 ሺህ 160 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም ገልጿል።

ከዚህ ውስጥ በጣሊያን 13 ሺህ 915 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በስፔን 10 ሺህ 348 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋልም ነው የተባለው፥ 211 ሺህ 856 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ተገልጿል።

በአሜሪካም በአንድ ቀን ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ግማሽ ያክሉ በአውሮፓ ይገኛሉም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.