Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የህወሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተሸብበው በሀሰት ዘገባ ላይ ተጠምደው እንደነበር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የህወሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተሸብበው በሀሰት ዘገባ ላይ ተጠምደው እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።
 
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በትግራይ ክልል የተወሰደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ትክክለኛ ገጽታ ወደጎን በመተው የህወሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተጠምደው የሀሰት ዘገባ ሲያሰራጩ እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኩል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ላይ ÷ ዓለም አቀፍ ሚዲያው የህወሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተሸብቦ የሀሰት ዘገባ ሲያሰራጭ እንደነበር በግልጽ የታየበት ሁኔታን መመልከት ተችሏል ብለዋል።
 
ይህ የሚዲያዎች ሁኔታ ትምህርት የተወሰደበት ነው ያሉት አቶ ደመቀ÷ በፕሮፓጋንዳ የተደገፈውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አስተሳሰብ ለመለወጥ ራሱን የቻለ ስራ እንደበነርም አብራርተዋል።
 
“ሁኔታው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በጁንታው የሐሰት መረጃ ተሸንፈው የፌደራል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ እንደሆነ መዘገባቸውን ያየንበትና ትምህርት የወሰድንበት ነው” ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
 
የዓለም አቀፍ ሚዲያው መሬት ላይ ያለውን እውነት ከመፈለግ ይልቅ የጁንታውን የሐሰት ወሬ በማራገብ የህግ ማስከበር እርምጃው ቡድኑን ለማጥቃት እንጂ ህግን ለማስከበር አይደለም በማለት የሀሰት መረጃ ሲያሰራጩ እንደነበር መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
 
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.