Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ትችያለሽ” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአዲስ አበባ “ትችያለሽ” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ተከበረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ “እለቱ ጾታን መሰረት ያደረጉ በደሎች እንዲቆሙ በቆራጥነት የምንሰራበት፣ ወንዶች የችግሩን አሳሳቢነትና አጣዳፊነት ተረድተው አጋርነታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት” ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም “ሚዛን የሳተውን ጾታዊ አድልዎ በቁርጠኝነት ለመዋጋት የሚያስችላቸውን ስልት የሚነድፉበትና ለተግባራዊነቱ ተግተው የሚሰሩበት፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የመፍትሄው አካል ሆነው፣ ከንግግር ባሻገር ተግባራዊ ውጤት የሚያስመዘግቡበት መሆን አለበትም” ነው ያሉት፡፡

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሴቶች የሚሳተፉት በድምፃቸው ለመምረጥ ብቻ ሳይሆን ከወንዶች እኩል ቁጥር ይዘው ለማስመረጥ እና በተመራጭነትም ሀገርን ለመምራት ጭምር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የብልፅግና ፖርቲም ይህንን እንደሚያረጋግጥ እርግጠኛ ነኝ ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ይህም የብልጽግና ማሳኪያ አንዱ አምድ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

“የሴቶች ቀንን ስናከብር በዚህ አዎንታዊ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነን ቃላችንም “ትችያለሽ እንችላለን” እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.