Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለማጥናት ወደ ውሃን ሊያቀኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለማጥናት ወደ ቻይና ውሃን ሊያቀና መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ቡድኑ 10 አባላትን የያዘ ሲሆን በቀጣይ ወር ነው ወደ ሁሃን ከተማ የሚያቀናው፡፡

የተመራማሪዎች ቡድን ወደፊት ዳግም ሊከሰት የሚችልን የቫይረሱን ወረርሽኝ ስርጭት መግታት በሚቻልበት አግባብ ላይ ይሰራል ነው የተባለው፡፡

ቤጂንግ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ለመስማማት ፈቃደኛ ባለመሆኗ  የዓለም ጤና ድርጅት ወደ ከተማዋ ይገባ ዘንድ ፈቃድ ለማግኘት ብዙ ወራቶች የፈጀ ድርድር አድርጓል ፡፡

ቫይረሱ በከተማዋ ከሚገኝ የእንስሳት ገበያ አካባቢ የመጣ ነው ተብሎ ይገመታል ፡፡

በሌላ በኩል  አሜሪካ እና አጋሮቿ ቫይረሱ በቻይና ላቦራቶሪ የተፈበረከ ነው በሚል ያቀረቡትን ውንጀላ ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል ውጥረት መንገሱ ይታወሳል፡፡

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ቻይና ወረርሽኙን ለመደበቅ እየሞከረች ነው ሲል ውንጀላ ማቅረቡም ይታወቃል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.