Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ተፈጥሯዊ የመስህብ ስፍራዎችን ለመጎብኘት ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ማዞር አለባቸው – ኤበን ዲስኪን

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ተፈጥሯዊ የመስህብ ስፍራዎችን ለመጎብኘት አይናቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያዞሩ ኤበን ዲስኪን የተባለው ፀሃፊ ገለፀ።

ለማታዶር ኔትወርክ ድረገፅ የሚጽፈው ኤበን በ35 ሀገራት ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች አፍሪካን ሲያስቡ ደቡብ አፍሪካ እና ግብፅን መዳረሻቸው ያደርጋሉ የሚለው ፀሃፊው እነዚህ ጎብኚዎች የአፍሪካን ሌሎች የመስህብ ስፍራዎች የማየት እድል ሳያገኙ መቅረታቸውንም ያነሳል፡፡

“አይናችሁን ወደ ምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ በማዞር ከዚህ በፊት ሊኖር ይችላል ብላችሁ ያልጠበቃችሁትን የተፈጥሮ መስህብ ታያላችሁ” ሲል ነው ያሰፈረው።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ በትግራይ ክልል ከተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ ውጪ በአፍሪካ ደህንነቷ የተጠበቀ እና የተረጋጋች ሀገር ናትም ብሏል።

ከጭስ አባይ ፏፏቴ ጀምሮ ምድር ላይ ያለ እስከ ማይመስለው አስደናቂው የዳሎል ዝቅተኛ ቦታ ድረስ ኢትዮጵያ ብዙ አስደናቂ ተፈጥሯዊ መስህብ የያዘች ሀገር መሆኗን አንስቷል።

ፀሃፊው በኢትዮጵያ ሊጎበኙ ከሚገባቸው አስደናቂ ተፈጥሯዊ ቦታዎች መካከል የሰሜን ተራሮች ፓርክ፣ ጭስ አባይ ፏፏቴ ፣የአርባ ምንጮች መፍለቂያ አርባ ምንጭ ከተማ፣ የዳሎል ዝቅተኛ ስፍራ፣ አዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ፣ የገራልታ ተራሮች እና የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተጠቃሾች መሆናቸውን በፅሁፉ ላይ አስፍሯል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.