Fana: At a Speed of Life!

“ዓድዋን እናንብብ” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት አደባባይ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ125ኛውን የአድዋ ድል በማስመልከት “ዓድዋን እናንብብ” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት አደባባይ ተከፈተ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፅሐፍት ኤጄንሲ የተዘጋጀው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 26 ቀን ይቆያል ተብሏል፡፡

በመርሀ ግብሩም ለህፃናት የሚሆኑ መፅሐፍትን በማዘጋጀት የህፃናት የንባብ ሳምንት እንዲሁም ዓድዋን በታሪክ አዋቂዎች ንግርት ተዘጋጅቷል።

በፕሮግራሙም ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እና ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.