Fana: At a Speed of Life!

ዕንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም – ጠ/ሚ ዐቢይ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም እንዲያውም የመሸጋገሪያ ድልድዮች ሆነው ያገለግሉናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ዓለማችን ላይ ቁልፍ ግኝቶች የተገኙት፣ አስደማሚ ቴክኖሎጂዎች የተሠሩትና ችግር ፈቺ መፍትሔዎች የተፈጠሩት በፈተና ጊዜ ነው።

በፈተና ጊዜ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዕንቅፋትን ወደ ዕድል ለመለወጥ በሚነሡ ብርቱዎች ትጋት እንደሆነ የብዙ ሀገራት የሥልጣኔ ታሪክ ያስተምረናል ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ሁላችንም ተረባርበን ይኼንን ወቅት ለመልካም ለውጥ ከተጠቀምንበት ያለ ጥርጥር መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆንበት ጊዜ ነው።

በምድር በሰማይ ብለን፣ ኃይላችንን አስተባብረን፣ ክፍተታችንን ሞልተን፣ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን፣ በኢትዮጵያ ጠላቶች ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናበሥራለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.