Fana: At a Speed of Life!

ዕውቀትና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ለይቶ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል – የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ዕውቀትና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ለይቶ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ በርካታ የማዕድናት ሃብት ክምችት እንዳላት ጠቅሶ ማዕድንን ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከአምስቱ የኢኮኖሚ የትኩረት መስኮች ማድረጉንም ነው ሚኒስቴሩ ያስረዳው፡፡

የማዕድናትን አለኝታ ቦታዎችና አይነት በጂኦሎጂካ ሰርቬይ ጥናት መሰረት መለየታቸውንም ገልጿል፡፡

በጥናቶቹ መሰረትም በኦሮሚያ ክልል ብረት፣ ወርቅ፣ ኤመራልድ፣ የድንጋይ ከሰል፣ ታንታለም፣ ላይምስቶን፣ ሳፋዬር፣ ፕላቲኒዬም፣ ማግኔታይት እንደሚገኙ ጠቅሷል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ብረት፣ ወርቅ እና ማርብል በስፋት እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በሌሎች ክልሎችም በተለያዩ አካባቢዎች የግንባታ፣ የጌጣጌጥ እና የከበሩ ማዕድናት በስፋት የሚገኙ ሲሆን በአማራ ክልል ኦፓል፣ ብረትና ግራናይት፤ በትግራይ ክልል የብረትና የወርቅ ማዕድናት ይገኛሉ፡፡

በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን መገኛ መሆኑ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በነዳጅ ዘርፍ በስድስት ብሎኮች የነዳጅ ክምችት ያላቸው መሆኑ በጥናት ተለይቷል፡፡

እነሱም የኦጋዴን፣ የስምጥ ሸለቆ፣ የጋምቤላ፣ የአባይ፣ የመተማ እና የመቀሌ የነዳጅ አለኝታ ቦታዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የኦጋዴን ካሉብና ሂላላ በተባሉ አካባቢዎች ፖሊጂሲኤል የተባለ ኩባንያ የሙከራ ምርት በማምረት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪ ኩባንያዎችን በላብራቶሪ፣ በፍለጋ፣ በምርመራና በልማት፣ በወርቅ ማጣራት እና በነዳጅ ቱቦ ዝርጋታ በማስገባት እና ለዜጎችና ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉን በሚገባ ለማልማት እና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.