Fana: At a Speed of Life!

“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በታላላቅ ስኬቶች ታጅቦ እየተፈጸመ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎች ሁለንተናዊ ድጋፍ በግንባር ከመዝመት በተጨማሪ በተለያዩ ድጋፎች ተጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በተሳሳተ መንገድ እንዲገነዘብ ለማድረግ የምእራቡ መገናኛ ብዙሃን የሚከተሉት አካሄድ ከእውነት የራቀ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ በመግለጫቸው ያነሱት፡፡
ለዚህም መንግሥት በአየርም ሆነ በመሬት ለትግራይ ክልል እያሰራጨ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ወደጎን ትተው ድጋፍ እንደሌለ የሚዘግቡበት መንገድ አንዱ ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡
በአንጻሩ የሽብር ቡድኑ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በፈጠረው ችግር ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማጓጓዝ እክል መፍጠሩን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃኑ ሲያነሱ አይሰማም ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ መንግሥት እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲሁም የሽብር ቡድኑ በወረራ በገባባቸው የአማራና አፋር ክልሎች እያደረሰ ያለውን ግፍ ሲዘግቡት አልተመለከትንም ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
ሲ ኤን ኤንን ጨምሮ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ‹‹ሁመራ ማሳክር›› ብለው በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት እንደተፈጸመ ሲያራግቡት የነበረው መረጃ ፍጹም ውሸት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የመገናኛ ብዙኃኑ በኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተ ዘገባቸውን እንደቀጠሉበት ጠቁመው÷ ለዚህም ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል እንዲሰበስቡና በማህበራዊ አገልግሎትም ጭምር ተሳታፊ እንዲሆኑ በማሰብ ለተወሰኑ ቀናት ትምህርት እንዲዘጋ ያደረገበትን በጎ ሀሳብ ቢ ቢ ሲ ‹‹መንግሥት ተማሪዎቹን ለጦርነቱ ማቀጣጠያነት ለመጠቀም ትምህርት ለማቆም ወስኗል›› ብሎ ፍጹም በተሳሳተ አካሄድ ለዓለም ማሰራጨቱን አንስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.