Fana: At a Speed of Life!

ዜጎቻቸው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የሚወተውቱ ሀገራት አስገርመውናል- የውጭ አገር ዜጎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች ተዘዋውረን ያለምንም ስጋት እየጎበኘን ነው፤ ዜጎቻቸው እንዲወጡ የሚወተውቱ አንዳንድ አገሮች ግን አስገርመውናል ሲሉ በጉብኝት ላይ ያሉ የውጭ አገር ዜጎች ተናገሩ።
 
ማርኮ ዳጋስፐር እና ማርክ ቻፕማን ኑሯችውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የውጭ አገራት ዜጎች መካከል ይጠቀሳሉ።
 
በቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩት ሁለቱ ጓደኛሞች በአስጎብኚ ድርጅታቸው በኩል ደንበኞቻቸውን እየያዙ በቱሪዝም መዳረሻዎች እየተዘዋወሩ በመጎብኘት ላይ ናቸው።
 
አዲስ አበባ አሁንም በነፋሻማዋ አየር የነፍስ ሃሴት የሚገበይባት፤ በሰላም ወጥተው አሻቸው ስፍራ ደርሰው የሚመጡባት ፍፁም ሰላማዊ ከተማ መሆኗንም ይናገራሉ።
 
ሰሞኑንም ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በ135 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ወንጪ ሃይቅ ሲጎበኙ አግኝተናቸዋል።
 
“ኢትዮጵያ የምወዳት ውብ ሀገር ነች፤ ባለፈው ሳምንት በአንኮበር እና በወልቂጤ ጉብኝት አድርጌያለሁኝ ሁሉም አካባቢ በጣም ሰላም ነው፤ ዛሬ ደግሞ ወንጪ እገኛለሁ፤ በተመለከትኩት ሁሉ ደስተኛ ነኝ” ይላል ማርክ ቻፕማን።
 
እውነታው ይህ ሆኖ እያለ አንዳንድ የምእራቡ ዓለም ሚዲያዎች በአዲስ አበባና አካባቢው ሰላም እንደሌለና የጦርነት ቀጠና በማስመሰል በሚያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ መገረሙን ገልጿል።
 
አዲስ አበባ ፍፁም ሰላማዊ ከተማ ነች፤ አንዳንድ አገሮች ግን ዜጎቻቸው እንዲወጡ ሲወተውቱ እንሰማለን፣ በዚህም ተገርመናል” ብለዋል ማርኮ ዳጋስፐር እና ማርክ ቻፕማን።
 
በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚሰማው ጦርነት በስተቀር በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ምንም አይነት ስጋት የለም እንደ ልብ መንቀሳቀስ ይቻላል ሲሉም ይናገራሉ።
 
በአዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች ተዘዋውረን ያለምንም ስጋት እየጎበኘን ነው፤ ዜጎቻቸው እንዲወጡ የሚወተውቱ አንዳንድ አገሮች ግን አስገርመውናል ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ ሰፊ አገር ነች፤ ወደ ሰሜን ጉዞ ማድረግ ባይቻልም በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎች ግን ፍፁም ሰላማዊ ነው፤ ማንም ሰው መንቀሳቀስና መጎብኘት ይችላል ሲሉም ይናገራሉ።
 
ኢትዮጵያን መጎብኘት የሚሹ የውጭ ዜጎች በርካታና ድንቅ የሆኑ ተፈጥራዊና ሰው ሰራሽ መስህቦቿን በነፃነት ተዘዋውረው መመልከት ይችላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በተለይም የ2021 የዓለም ተመራጩ የኢኮ ቱሪዝም መንደር በሚል በዓለም ቱሪዝም ድርጅት የተመረጠው ወንጪ ሐይቅ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ያለ ማራኪ መዳረሻ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.