Fana: At a Speed of Life!

ዜጎች የአካላዊ ርቀት ህጎችን እንዲያከብሩ የሚያሳውቀው የሮቦት ውሻ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በሲንጋፖር ከኮሮቫ ቫይረስ ጋር በተያያዘ ዜጎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ የሚያስገድደው የሮቦት ውሻ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ መሰማራቱን ተሰምቷል።

የሮቦት ውሻው የተጠጋጉ ሰዎችን ርቀታቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ከማስተላለፍ ባሻገር ለዚሁ አላማ በተገጠመለት ካሜራና ሴንሰር መልዕክቱ ምን ያህል ሰዎች ጋር ተደራሽ እንደሆነ ለመገመትና ከኮቪድ 19 ወረርሽን ጋር በተገናኘ በየፓርኩ የሚመጡ ሰዎችን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል፡፡

የሮቦት ውሻው ለሁለት ሳምንታት ለሙከራ በተሰማራበት ስፍራ ”ለእርስዎና በአካባቢዎ ለሚገኙ ሰዎች ደህንነት ሲባል እባክዎትን ቢያንስ አንድ ሜትር ተራራቁ ፤ አመሰግናለሁ!” የሚል መልእክት ሲያስተላለፍ ነበረም ነው የተባለው።

ይህ የውሻ ሮቦት የተሰራው መቀመጫውን አሜሪካ ባደረገ ቦስተን ዳይናሚክስ በተባለ የኢንጅነሪንግና ሮቦት ዲዛይን ካምፓኒ ነው ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግሥት የሮቦቱ ካሜራዎች በግለሰቦች ላይ ክትትል የማያደርጉና የግል መረጃዎችንም የማይሰበስቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሮቦቱ በሰዓት 5ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ የሚችል ሲሆን ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ቢወድቅም ድጋሚ በመነሳት ተግባሩን እንደሚቀጥል ነው የተነገረው፡፡

ሲንጋፖር በእስያ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁባት ሃገር መሆኗም ይነገራል።

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.