Fana: At a Speed of Life!

ዢ ጂንፒንግ ቻይና በገጠራማ አካባቢዎች ድህነት ላይ ድል መቀዳጀቷን አወጁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸው በገጠራማ አካባቢዎች ድህንትን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን አወጁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ98 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከድህነት መላቀቃቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

በሀገሪቱ በድህነት ውስጥ የነበሩ 832 አውራጃዎች እና 128 ሺህ መንደሮች ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ወጥተዋል ብለዋል፡፡

ቻይና በገጠራማ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ4 ሺህ ዩዋን ወይም ከ619 የአሜሪካ ዶላር በታች ገቢ ያላቸውን ዜጎቿን ድህነት ውስጥ የሚገኙ በማለት ታስቀምጣቸዋለች፡፡

የዓለም ባንክ በበኩሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ693 የአሜሪካ ዶላር በታች የሆኑትን የድህነት ወለል ወሰን አድርጓል፡፡

በጥቅሉ ቻይና በተመሳሳይ ወቅት ዓለም ላይ ከ70 በመቶ በላይ ለድህነት ቅነሳው አስተዋጽኦ ማበርከቷን ገልጻለች፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.