Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል መስተዳድር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፈ፡፡

መስተዳድሩ በዓሉን ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክርና የክልሉን ሰላምና ልማት በማጠናከር ማክበር እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

ካለፉት አመታት አንፃር በተለይም የዘንድሮው አመት የክልሉ ህዝብና መንግስት ፊቱን ወደ ልማት ያዞረበት እና የልማት እንቅስቃሴዎች በተጨባጭ እየተስተዋለ ያለበት አመት መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ባሻገር ህብረተሰቡ ኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንፃር እያሳየ ያለውን መዘናጋት በመቅረፍ ቫይረሱ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ መቀነስ ያስፈልጋልም ብሏል፡፡

ለዚህም በዓሉን ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ በጥንቃቄ ማክበር ይገባልም ነው ያለው፡፡

ዘመናት ያስቆጠረውን በሰላም በፍቅርና በአብሮነት የመኖር እሴት ማጠናከር ከሁሉም የክልሉ ነዋሪ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ህዝበ ክርስቲያኑ የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብርም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.