Fana: At a Speed of Life!

የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ታምሩ ተፈሪ እንደገለጹት÷ ከከተማዋ የተለያዩ ገቢዎች 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ስራ ተጀምሯል፡፡

ባለፈው ዓመት 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ሃላፊው አስታውሰዋል፡፡

የሩብ ዓመቱ አፈጻጸምም 85 ከመቶ ላይ መድረሱን ነው አቶ ታምሩ የተናገሩት፡፡

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋ ገቢ ከዓመት ዓመት እየተሻሻለ ቢመጣም ገቢው ከተማዋ ካላት አቅም አንፃር የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ፣ አለመመዝገብ ፣ታክስን አለማሳወቅና አሳንሶ መክፈል የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል።

በተለይም በከተማዋ የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ግብር የማይከፈልበት ዘርፍ እንደሆነ መለየቱን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

 

በመቅደስ አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.