Fana: At a Speed of Life!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ለ15ኛ ዙር ፤ በህክምና ስፔሻሊቲ ያሰለጠናቸውን ደግሞ ለ6ኛ ዙር አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 246 ቅድመ ምረቃ ፣ 74 በ2ኛ ዲግሪና እና 40 የህክምና ስፔሻሊስቶችን ጨምሮ 360 ተማሪዎችን ማስመረቁን የኮሌጁ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ጋዲሳ ተናግረዋል፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አያኖ ባራሶ ፥ ተመራቂዎቹ በታማኝነትና በቅንነት ሃገራቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተመራቂዎች በብዙ ፈታኝ መንገዶች በማለፍ ለምረቃ በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ፥ በአገሪቱ ያለውን የህክምና አገልግሎት ክፍተቶች ለመሙላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው፥ በተሰማሩበት ሙያ ማህበረሰቡን በታማኝነት እና በቅንነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በታመነ አረጋ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.