Fana: At a Speed of Life!

የሀይማኖት ተቋማት በቤተ እምነቶች የሚደረጉ ሀይማኖታዊ ስርአቶች እንዲቆሙ በመወሰናቸው ኢ/ር ታከለ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀይማኖት ተቋማት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት በቤተ እምነቶች የሚደረጉ ሀይማኖታዊ ስርአቶች እንዲቆሙ በመወሰናቸው እንዲሁም አዳራሽና ቦታቸውን መንግስት እንዲጠቀምበት በመፍቀድ ላሳዩት ቀና ተግባር ኢ/ር ታከለ ምስጋና አቀረቡ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሀይማኖት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በቀጣይም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎች በህብረተሰቡ እንዲከበሩና ሀይማኖታዊ ተግባራትም በቤት እንዲተገብር የሀይማኖት መሪዎች ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ ኢ/ር ታከለ የሀይማኖት መሪዎቹን ጠይቀዋል።

በቀጣይ በሁሉም እምነት ተከታዮች የሚተገበር የጋራ ጸሎት እንዲታወጅ እንደሚያደርጉ የሀይማኖት መሪዎቹ አሳውቀዋል ለተፈፃሚነቱም መንግስት ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል።

ህብረተሰቡ በቤቱ ሆኖ ሀይማኖታዊ ተግባራትን እንዲከውንና እንዲከታተል ከነገ አርብ ጀምሮ የጁምአ ሶላትን ጨምሮ የተለያዩ ሀይማኖታዊ መርሀ ግብሮች በአዲስ ቲቪ እንዲተላለፉ እንዲደሚደረግም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.