Fana: At a Speed of Life!

የሄፒታይተስ በሽታ ስርጭት ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን መጠብቅ አለበት- የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሄፒታይተስ (የጉበት በሽታ) እንደ ሌሎች በሽታ አጀንዳ ሆኖ ብዙ ባይሰራበትን ስርጭቱ ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ከዚህ ቫይረስ ሊጠብቅ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ አሳሰቡ።

ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ዱጉማ  ዛሬ አለም አቀፍ የሄፓታይተስ ቀን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሄፓታይተስ በሽታ አሁን ላይ ከአለም በገዳይነቱ በ2ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በመሆኑም መንግስት ከመቼውም በላይ  በሄፒታይተስ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው መሆኑንም አስታውቅዋል።

በዚህም ቫይረሱን ለመከላከል ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ተጋላጭ ለሆኑ ከ675 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ክትባት መሰጠቱ ተጠቁሟል።

ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ በመደበኛ የክትባት መርሃግብር ተካቶ ለህጻናት እየተሰጠ ነውም ተብሏል።

ዛሬ አለም አቀፍ የሄፓታይተስ ቀን በአለም ለ10ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ “ከጉበት በሽታን ነጻ የሆነን ነገን እንፍጠር”  በሚል መሪ ቃል እናቶች እና ህጻናት በጉብት በሽታ እንዳይያዙ በሚደረግ ጥረት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል ተብሏል።

በአለም በየአመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች በሄፓታይተስ በሽታ እንደሚሞቱ መረጃዎች ያመካክታሉ።

በሃኢትዮጵያም  በሽታው በስፋት ከተሰራጨባቸው ሀገራት ስትመደብ በ2017 በተሰራ ጥናት 9 ነጥብ 4 በመቶ በሄፓታይተስ ቢ እንዲሁም 3 ነጥብ 1 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ሄፓታይተስ ሲ እንዳለባቸው ይገመታል።

በሀይማኖት እያሱ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.