Fana: At a Speed of Life!

የሄፓታይተስ ”ሲ” ቫይረስን ያገኙ ተመራማሪዎች በህክምናው ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጉበትን የሚጠቃው የሄፓታይተስ ”ሲ” ቫይረስን ያገኙ ሶስት ተመራማሪዎች በጋራ የ2020 የህክምናው ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ።

ይህን ሽልማት በጋራ ያሸነፉት የብሪታንያው ተመራማሪ ሚካኤል ሀውተን እና አሜሪካዊያኑ ኸርቬይ አልተር እንዲሁም ቻርለስ ራይስ ናቸው።

የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ተመራማሪዎቹ የብዙ ሚሊየኖችን ህይወት የሚታደግ ግኝት በማበርከታቸው የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል ብሏል።

በተጨማሪም በታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሽታው አሁን ሊድን የሚችል በመሆኑ ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስን ከዓለም የማጥፋት ተስፋን ከፍ ያደርገዋልም ነው ያለው ።

ሄፓታይተስ “ሲ” ለጉበት ካንሰር የሚዳርግና በርካታ ህሙማንን የጉበት ንቅለ ተከላ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ነው ተብሏል።

በዓለም ላይ በዚህ በሽታ የተያዙ 70 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ሲገኙ በዓመት እስከ 400 ሺህ ሰዎችን ለህልፈት እንደሚዳርግም ተገልጿል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.