Fana: At a Speed of Life!

የህብረት ባንክ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ፣ይሸለሙ” የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ሕብረት ባንክ የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተከናውኗል።
መርጋ ግብሩ ሕብረት ባንክ ላለፉት ስድስት ወራት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬን በባንኩ ለሚቀበሉና ለሚመነዝሩ ደንበኞች ያዘጋጀው መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም መሰረት ከታህሳስ 5 ቀን እስከ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው የይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸለሙ መርሃ ግብር ላይ አሸናፊ የሆኑት የዕጣ ቁጥሮች ወጥተዋል።
በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ የቢዝነስና ኦፐሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚን ጨምሮ የባንኩ የስራ ኃላፊዎች፣ የብሔራዊ ሎተሪ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ የቢዝነስና ኦፐሬሽንስ ም/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፅገሬዳ ተስፋዬ÷ በሎተሪው በመርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ደንበኞችን አመስግነው÷ ይህ መርሃ ግብር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ ረገድ ለኢኮኖሚው የራሱን ድርሻ የሚያበረክት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አያይዘውም ከውጪ የተላከላቸውን የዉጭ ምንዛሬ በባንኩ የተቀበሉ እና የመነዘሩ ደንበኞችን ለመሸለም የተዘጋጀው የሎተሪ ማውጣት ስነ ስርዓት ደንበኞችን ይበልጥ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.