Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ጁንታ በግዳጅ ያሰለፋቸው የጥፉት ሀይሎች በአፋር እና በአማራ ክልል በኩል እጅ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የህወሓት ጁንታ በግዳጅ ያሰለፋቸው የጥፉት ሀይሎች በአፋር እና በአማራ ክልል በኩል ከግንባር እየጠፉ እጅ እየሰጡ ይገኛሉ።

የህወሓት ቡድን የትግራይን ህፃናት እና ወጣቶች አሰገድዶ ወደ ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን ምርኮኞቹ ገልፀዋል ።

ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ቤተሰቦቻችን ሳያውቁ ከመንገድ ላይ ተወስደን የስምንት ቀን ስልጠና ወስደን ወደ ጦርነት ማገደውናል ያሉት ምርኮኞቹ ÷ ሆኖም ከነበርንበት ግንባር በአፋር እና በአማራ አካባቢዎች እጃችንን ሰጥተናል ብለዋል።

ምርኮኞቹ እንደኛ በርካታ ጓደኞቻችን እጅ ለመስጠት በየጫካው አሉ ያሉ ሲሆን÷ አሁን ላይ እጃችንን ሰጥተን በጥሩ ሁኔታ እንገኛለን ማለታቸውን ከአፋር መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.