Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ጁንታ ደቡብ ሱዳን የተረጋጋች ሀገር እንዳትሆን ሲሰራ ነበር- የሀገሪቱ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት ጁንታ ደቡብ ሱዳን የተረጋጋች ሀገር እንዳትሆን ሲሰራ መቆየቱን በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒታ ሞርጋን ገለፁ።

አምባሳደር ጀምስ ፒታ ሞርጋን እንደገለፁት፥ የህወሓት ጁንታ አባል አንዱ በሆኑት አምባሳደር ስዩም መስፍን ዋና አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት አልቻለም።

ምክንያቱ ደግሞ የህወሓት ቡድን ለሀገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች በነበረው አድሏዊ አቋም ነው ሲሉም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

በፈረንጆቹ 2015 የተፈረመው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ መሆን አለመቻሉን ያስታወሱት አምባሳደር ጀምስ፥ ለዚህ ደግሞ አምባሳደር ስዩም ያሳዩት ወገንተኝነት ምክንያት ነው ብለዋል።

በህወሓት ጁንታ አባል ዋና አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትም አስፈላጊውን ውጤት ሳያመጣ ቀርቷልም ነው ያሉት አምባሳደሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉትንግግር የህወሓት ጁንታ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ሂደት ላይ የነበረውን አሉታዊ ሚና ይፋ ማድረጋቸው እንዳስደሰታቸው አንስተዋል፡፡

የህወሓት ጁንታ ቡድን በሰላም ድርድሩ ላይ የነበረው የተዛባ አመለካከት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት የጎዳ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ ደቡብ ሱዳን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ትተማመናለች ያሉት አምባሳደሩ፥ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መንገድ በመፍታት ወደ ልማት ስራዎች እንደምትመለስ እምነታቸውን ገልፀዋል።

አምባሳደር ጀምስ አክለውም፥ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ያለው ግንኙነት ጠንካራ ደረጃ ላይ መድረሱንም አስታውቀዋል።

“ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ከሀገሯ እንዲወጡ አዘዘች”በሚል በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተሰራጨውን ሀሰተኛ መረጃ አስመልክቶም አምባሳደር ጀምስ መረጃው በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሀይሎች የተፈበረከ መሆኑን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት እንዲነግስ ካላቸው ፍላጎት የመነጨ ነው ብለዋል።

በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሀይሎች እንዲህ አይነት የሀሰት ዜናዎችን የሚያሰራጩት ወደ እነ አምባሳደር ስዩም መስፍን ዘመን ለለመስ ካላቸው ፍላጎት የመነጨ መሆኑንም ከኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.