Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ በመስክ ጉብኝት ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ በመስክ ጉብኝት ተገመገመ፡፡

የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በስፍራው በመገኘት ገመገሙ፡፡

በግምገማቸውም መሰረት የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ተመልክተዋል፡፡

ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራተሮች፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.