Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ በተመለከተ የሶስተኛ ሀገራት መሪዎች አስተያየት የኢትዮጵያን ታሪክ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው- የእስራኤሉ ምክትል የደህንነት ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚረባረቡበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልቶ የሶስተኛ ሀገራት መሪዎች አስተያየት የኢትዮጵያን ታሪክ ካለማወቅ የሚነጭ ነው አሉ የእስራኤል ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ጋዲ ይባርከን።

ምክትል ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳብራሩት ዓባይ ለኢትዮጵያዊያን ወንዝ ብቻ ሳይሆን የእምነት ፣ ፍልስፍናቸው ምንጭ እና የታሪካቸው አንድ አካል ነው ብለዋል።

አሁን  ላይ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆኑ ዜጎች ሳይቀሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እየተረባረቡበት በሚገኘው ግድብ ዙሪያ ከሶስተኛ ወገኖች የሚሰጡ አፍራሽ አስተያየቶች የሀገሪቱን ታሪክ በሚገባ ካለማወቅ የሚመነጩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

እርሳቸው እንደ አንድ ትውልደ ኢትዮ እስራኤላዊ  የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ በድህነት የሚማቅቁ ዜጎችን ህይወት ይቀይራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ተሰናባቹ ለመባል ጥቂት ጊዜ የቀራቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰጡትን አስተያየት በግላቸው እንደሚያወግዙ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ምክትል ሚኒስትሩ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ላይ እንደ አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ አንድ ሺህ ዶላር ለመስጠት እና ሌሎች ቤተ እስራኤላዊያንን ለማስተባበር ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።

በስላባት ማናዬ እና ባህሩ ይድነቃቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.