Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት ታህሳስ 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳሉ።

ውይይቱ የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተገኙበት እንደሚካሄድ ነው የተነገረው።

ይህ የቴክኒክ ስብሰባ በግድቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ፣ ካይሮ ፣ ካርቱም እንዲሁም በዋሽንግተን መካሄዱ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.