Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመር ማብሰሪያ ሥነ ስርአት ተካሂዷል።

በዛሬው እለት ስራ የጀመረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን፥ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው።

ባለፈው የካቲት ወር ላይ 270 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ዩኒት10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 540 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

ይህም ጊቤ 1 እና ጊቤ 2 በጋራ የሚያመነጩትን የኤሌክትሪክ ኃይል ማለት ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን ባለው ከፍታና በያዘው የውሃ መጠን ዛሬ ስራ የጀመረውን ጨምሮ እያንዳንዱ ተርባይን 270 ሜጋዋት የአሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ይችላሉ።

ግድቡ በሙሉ አቅሙ ሃይል ማመንጨት ሲጀምር ደግሞ እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ሃይል የሚያመነጭ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.