Fana: At a Speed of Life!

የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራችን ሳይጠናቀቅ ከመቐለው ጁንታ ጋር ድርድር አይኖርም-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ ሳይጠናቀቅ ከመቐለው ጁንታ ጋር ድርድር እንደማይኖር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእት፥ “ስግብግቡና አረመኔው የመቐለ ጁንታ በሰሜን ኮማንድ አባላት ያደረሰውን ኢሰብአዊ ግድያ፣ ግፍ እና በደል መቸውንም አንረሳውም” ብለዋል።

“ይህ ጁንታ ለፍትህ ቀርቦ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ ለአፍታም ቢሆን አናርፍም” ሲሉም ገልፀዋል።

“አሁንም ደግሜ ለኢትዮጵያውያን ላረጋግጥላችሁ የምወደው የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራችን ሳይጠናቀቅ ከዚህ ጁንታ ጋር ድርድር እንደማይኖር ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልእክታቸው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.