Fana: At a Speed of Life!

የለገዳዲ ክፍል ሁለት የውሃ ፕሮጀክት ከቀጣይ አመት ጥቅምት ወር  ጀምሮ የመጠጥ ውሃ ስርጭት እንዲጀምር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ልማት ፕሮጀክት ከቀጣይ አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ የመጠጥ ውሃ ስርጭት አገልግሎት  እንዲጀምር በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ከሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በለገዳዲ ክፍል ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ልማት ፕሮጀክትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ልማት ፕሮጀክት በ17 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች 86 ሺህ ሜትር ኩብ ውሃ ያመርታል።

የውሃ ፕሮጀክቱ የምስራቅ ሰሜን አዲስ አበባ በተለይ የካ እና የጉለሌ ክፍለ ከተሞችን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን እንደሚቀርፍ  ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የለገዳዲ የውሃ ፕሮጀክት ጉብኝት ለግድቡ ጥገና ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ መሆኑን በጥናት በመቅረቡ ለውሣኔ ያመች ዘንድ ያለበትን በአካል ለማየት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በወይዘሮ አዳነች የተመራው የልዑካን ቡድን በአቃቂ እየተገነባ ያለውን የከርሠ ምድር ውሃ ፕሮጀክትም ጎብኝቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.