Fana: At a Speed of Life!

የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መገበያያ ማዕከል ላይ እሳት የመለኮስና ሱቆቹን የማፍረስ ሙከራ ያደረጉ ሰዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መገበያያ ማዕከል ላይ እሳት የመለኮስና ሱቆቹን የማፍረስ ሙከራ ያደረጉ ሰዎች ተያዙ፡፡
አዲሱን የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መገበያያ ማዕከል ግልጋሎት ለማወክ የሚሰሩ ጥቂት ግለሰቦች ቦታው ላይ እሳት የመለኮስና ሱቆቹን የማፍረስ ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸው ተገለጸ።
“በከተማችን ውስጥ ህጋዊነትን ማስያዝ የግድ ነው” በማለት የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክረታሪያት፤ የአትክልት ተራ ከፒያሳ የመነሳትና በጃንሜዳ በጊዜያዊነት እንዲቆይ የመደረጉ ምክንያት አለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል መሆኑን አስታውሷል።
ጃንሜዳ ወደቀደመው ማህበራዊ ግልጋሎት ለመመለስና ለጥምቀት በዓልም በማስለቀቅ፤ 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ የንግድ ማዕከል በማስገንባት በውስጡም በቂ የመኪና ማቆሚያና ምቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ 556 ጥራታቸውን የጠበቁ ሱቆች፣ የምግብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችና የንፅህና መጠበቂያ ስፍራ ተገንብቶለት ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሷል።
ነገር ግን “ከጃንሜዳ መነሳት የለብንም፤ ወደ ፒያሳ እንመለስ” በሚሉ ጥቂት በህቡዕ የተደራጁ ነጋዴና ከነጋዴ ውጪ ባሉ አካላት የተለያዩ ጥፋቶች (እሳት የመለኮስና ሱቁን የማፈረስ ) ሙከራ ሲያደርጉ ተይዘዋል።
“ይህንን የህዝብ ሀብት ያፈሰስንበትን ዘመናዊ የንግድ ማዕከል በአግባቡ በመጠቀም ለጤናማው ነጋዴና ስለብዙሀኑ የሸማች ማህበረሰብ ስንል ንፅህናውና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ግልጋሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይኖርብናል” ብሏል።
“ሌሎች ተመሳሳይ ማዕከላት እየገነባን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን እንጂ ወደኋላ መመለስ የለብንም” ያለው ፕሬስ ሴክሬታሪያቱ፤ ህብረተሰቡ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማንኛውንም ህገወጥ ድርጊቶች በመከላከልና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም በትብብር እንዲሰራና እንዲያጋልጥ ጥሪውን አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.