Fana: At a Speed of Life!

የሌሶቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ከባለቤታቸው ግድያ ጋር በተያያዘ ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሌሶቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማሳ ታባኔ ከባለቤታቸው ግድያ ጋር በተያያዘ ሥልጣናቸውን ሊለቁ መሆኑ ተሰማ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ 2017 ከተፈጸመው የባለቤታቸው ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የሚል ውንጀላ መበራከቱን ተከትሎ ነው ስልጣናቸውን ይለቃሉ የተባለው።

ከእርሳቸው በዓለ ሲመት ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ባለቤታቸው የተገደሉ ሲሆን፥ በወቅቱ ከሟች ባለቤታቸው ጋር ጋር ፍቺ ለመፈጸም እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር ተብሏል።

ታባኔ የሚመሩት ኤቢሲ ፓርቲም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ግፊት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

የፓርቲው አንጋፋ አባላትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግድያው ጋር በተያያዘ እየተደረገ ያለውን ምርመራ እያስተጓጎሉ ነው በሚል ወንጅለዋቸዋል።

ፖሊስም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በወቅቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረጉ የስልክ ልውውጦች መያዙን ገልጿል።

የኤቢሲ ቃል አቀባይ ሞንቶኤሊ ማሶኤትሳ ደግሞ ታባኔ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

ፓርቲው በቀጣይ በፓርላማ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሰይም ይሆናልም ነው ያሉት።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.