Fana: At a Speed of Life!

የሌጎስ አስተዳዳሪ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጀሪያ ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ የሌጎስ አስተዳዳሪ ባባጂዴ ሳንዎ ኦሉ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ናይጀሪያውያን ከሰሞኑ ፖሊሶች የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡

በትናንትናው ዕለትም የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ሌጎስ የወታደር ዩኒፎርም የለበሰ ግለሰብ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈቱ ነው የተነገረው፡፡

በዚህ ሳቢያም የሰው ህይወት ማለፉን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

የከተማዋ አስተዳዳሪም በግለሰቡ የተከፈተውን ተኩስ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ተኩሱ ከእነሱ ቀጥተኛ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ኃይሎች መፈጸሙን ጠቅሰው አንድ ሰው መሞቱንና 28 ሰዎች መቁሰላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

አስተዳዳሪው ለተቃውሞ አደባባይ የወጡትን በመደገፍ ለሦስት ቀናት አስተዳደራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ አዘዋል፡፡

በተጨማሪም ለሦስት ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓለማ በግማሽ እንዲውለበለብ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.