Fana: At a Speed of Life!

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል ሠልጣኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል የ33ኛ ዙር መሠረታዊ የኮማንዶ እንዲሁም 10ኛ ዙር መሠረታዊ የልዩ ኃይል እና ፀረ ሽብር ሠልጣኞችን አስመረቀ።

ሥነ ሥርዓቱም የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

ተመራቂዎቹ የጠላትን ማዘዣ አጥቅቶ የመመለስ ትርዒት ማሳየታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.