Fana: At a Speed of Life!

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የ33ኛ ዙር መሠረታዊ የኮማንዶ ሰልጣኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የ33ኛ ዙር መሠረታዊ የኮማንዶ ሰልጣኞችን አስመርቋል ።
ተመራቂዎቹ ሁለት ሻለቃ ሲሆኑ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ግዳጆችን በብቃት መወጣት የሚያስችል ክህሎች መጨበጣቸው ተገልጿል።
የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሹማ አብደታ ባደረጉት ንግግር ÷ የክፍላችን የሠራዊት አባላት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተካሄደው ዘመቻ የሰሯቸው ገድሎች አንፀባራቂ ናቸው ብለዋል ።
አያይዘውም በወታደራዊ ሳይንስ የተካኑት የልዩ ዘመቻዎች ሀይል አባላት ፣ ጁንታው የሚመካበትን ምሽግና የታጣቂ ሀይል ስብስብ በመደምሰስ ለወገናቸው ድል አብስረዋል ነው ያሉት።
የዛሬ ተመራቂዎችም የክፍላችሁን አንፀባራቂ ታሪክ ለመጠበቅ ፣ በቅብብሎሽ ወደር የሌለው ጀግንነትን መፈፀም እንደምትችሉ አልጠራጠርምም ነው ያሉት ።
ታሪክ በመስራት የታሪኩ ባለቤት ለመሆን እነሆ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሳችኋልም ሲሉ ገልጸዋል ።
የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ተዝገራ ከበደ በበኩላቸው ÷ ተመራቂዎች ፣ ተኩስን በመጠቀም የተለያዩ የመሬት ገፆች ፣ በቀንና በሌሊት የሚጠይቁትን ስልታዊ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ፣ መደበኛ የሆኑና ያልሆኑ ግዳጆችን ከጠላት ፊትና ጀርባ መፈፀም የሚ ያስችል አቅም ፈጥረዋል ማለታቸውንከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.