Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 37ኛ እና 38ኛ ዓመታዊ የምርምር ስርአትና ማህበረሰብ ተሣትፎ ጉባኤ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 37ኛ እና 38ኛ ዓመታዊ የምርምር ስርአትና ማህበረሰብ ተሣትፎ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩ በአምስት ዘርፎች ስር የተጠናቀቁ 75 የምርምር ስራዎች ለምሁራን ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ኮቪድ-19፣ በማህበረሰብ አገልግሎት የተሰሩ የምርምር ስራዎችና የማህበረሰብ አገልግሎቶች ቀርበው ግምገማ ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የተሰሩት ጥናትና ምርምሮች ወደ ህብረተሰቡ ወርደው እንዲያገለግሉ ዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

በሚጠናቀቀው መድረክ ምርምሮቹ በአለም አቀፍ ጆርናሎች እንዲታተሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የመስጠት ስነ- ስርአት ይከናወናልም ነው የተባለው።
37ኛው መርሐ ግብር አምና መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በኮቪድ-19 ምክንያት አልተካሄደም።

በቲያ ኑሬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.