Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ከሰኞ ጀምሮ ጉባኤውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አስታወቁ።
 
አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንደገለጹት ለሁለት ቀናት የሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ የ2012 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
 
ለክልሉ የ2013 የስራ ዘመን ማስፈጸሚያ ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ አባላት ይቀርባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
የቀረቡትን የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና ረቂቅ በጀቱ ላይ የምክር ቤቱ ከተወያየበት በኋላ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።
 
እንዲሁም የምክር ቤቱ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላትን የቀጣይ ስራ ትኩረት አቅጣጫ እንደሚመለከት የገለጹት አፈ ጉባኤዋ አዳዲስ ሹመቶች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.