Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች “ደማችን ለወገናችን” በሚል መርህ የደም መስጠት መርሐ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባለትና የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች “ደማችን ለወገናችን” በሚል መርህ የደም መስጠት መርሐ ግብር አከናወኑ።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የምክር ቤቱ አፈ-ጉበዔ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ፣ የምክር ቤቱ አባላትና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊዎች እንዲሁም ሰራተኞች ደም ለግሰዋል።
ዓላማውም በሀገራችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የደም ባንክ አገልግሎት የደም እጥረት አጋጥሞኛል በማለት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ፕሮግረሙን ያስጀመሩት የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ተደሰ ገልጸዋል፡፡
ከብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የመጡት ሲስተር እንግዳወርቅ አባተ በበኩላቸው÷ በተከሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም የምክር ቤቱ ኃላፊዎችና አባላት እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ህዝባዊ ውግንናቸውን ለመግለፅ ውድ የሆነውን ደማቸውን ለወገናቸው ለመለገስ ላሳዩት ተሳትፎ ምስጋናቸውን በማቅረብ ሁሉም ዜጋ በዚህ በጎ ተግባር ሊሳተፍ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባላትም በህገ-መንግስቱ የተጣለብንን ትልቅ ኃላፊነት በትጋት ከመወጣት ባሻገር የኮሮና ወረርሽኝ በተከሰተ ግዜ አቅም በፈቀደ መጠን ከመረጠን ወገናችን ጎን እንቆማለን ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ሊያጋጥም የሚችለውን የደም እጥረት ታሳቢ በማድረግ በእንደዚህ መሰል በጎ ተግባር አጋርነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.