Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ የወደመባቸው የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አርሶ አደሮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ከውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተዋቀረ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በአንበጣ መንጋ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አከባቢዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ ባለፈም ከስሬ ሳዶ ቀበሌ አርሶ ደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም ሆነ በመስክ ምልከታው በደረሱ የማሽላ፣ የገብስ፣ የበቆሎ እና በእንስሳት መኖዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱራህማን አብደላ እንዳሉት ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በዞኑ ከሚገኙ 15 ወረዳዎች መካከል በ11 ወረዳዎች ላይ መታየቱንና በዚህም 190 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

እንዲሁም ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ከአርሶ አደሩ እንዲሁም ከወረዳ እስከ ፌደራል ካለው መዋቅር ጋር በመቀናጀት የባህላዊ መከላከያ ዘዴዎችን እና የአውሮፕላን ርጭት በመጠቀም የመንጋውን እንቅስቃሴ መቆጣጠር እና ዞኑን ሙሉ በሙሉ ከበረሃ አንበጣ ነጻ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም የመስኖ አማራጮችን በመጠቀም መልሶ ማልማት የሚችሉት ማሳዎች እንዲለሙ፤ በደረሰባቸው ውድመት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ደግሞ በቴክኒክ ባለሙያዎች ተለይተው በሚቀርበው መረጃ መሰረት ድጋፍ ለማድረግ የፌደራል መንግስት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.