Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነገ በሚያካሂደው ስብሰባው የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ ይጀምራል ተብሎ የጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እንደሚያዳምጥ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.