Fana: At a Speed of Life!

የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመላው ሃገሪቱ ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ እንሚጠናቀቅ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በሲዳማ ክልል እንዲሁም ሶማሌ ክልል የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ ድምጽ መስጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ለዜጎች መረጃ የሚያቀርቡ ሚዲያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የምዝገባ የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ ዜጎች ካርዳቸውን እንዲወስዱ ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.