Fana: At a Speed of Life!

የመሬት ወረራን ለመከላከል የካዳስተር ትግበራን እውን ማድረግ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት እና ሕገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል አመራሩ በተጠያቂነት አግባብ የካዳስተር ትግበራን እውን እንዲያደርግ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ሚኒስቴር የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2015 የዕቅድ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ሕገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የመሬት ምዝገባና የካዳስተር ስርዓትን መተግበር እንደሚገባ አጽንዖት መሰጠቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ÷ በከተሞች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አመራሩ ከሌብነት በጸዳ አግባብ አዳዲስ ሐሳቦችን እያፈለቀ ዘመናዊ አሠራርን እየዘረጋ በቁርጠኝነትና በታማኝነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የሲቪክና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ ÷ በምርጫ ወቅት ለህብረተሰቡ የተገባነው ቃል ሳይዘነጋ ለዜጎች ጥያቄ አመራሩ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ለዚህም ፓርቲው ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን በሰጡት ማብራሪያ÷ ሚኒስቴሩ ፖሊሲዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን፣ ክትትልና ድጋፎችን፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንዲያከናውን በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሠረት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣና ክልሎችም የራሳቸውን ድርሻ በተገቢው መንገድ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.