Fana: At a Speed of Life!

የመርሐ ጋርመንት ፋብሪካ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው – ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሐ ጋርመንት ፋብሪካ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ አልባሳት ምርቶችን ለመተካት እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የመርሐ ጋርመንት ፋብሪካ የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ ፋብሪካው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ አልባሳት ምርቶችን ለመተካት እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ለ300 ሰዎች ቋሚ የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ በሙሉ አቅሙ ወደሥራ ሲገባ ለ1 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.