Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል ህብረሰተቡን ከኮሮና ቫይረሰ ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ፤ በመስቀል አደባባይ እንደሚከበር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚከበረው የመስቀል በዓል ህብረሰተቡን ከኮሮና ቫይረሰ ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ በመስቀል አደባባይ እንደሚከበር ተገለፀ።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክድ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የመስቀል አደባባይን መልሶ ግንባታ ፕሮጄክት የደረሰበትን ደረጃ ዛሬ ተመልክተዋል።
 
በጉብኝቱም ሌሎች የከተማዋ የከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የቤተክርስቲያኗ የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል፡፡
 
መጪው የመስቀል ደመራ በዓል አነሰተኛ ምእመናን በተገኙበት በመስቀል አደባባይ እንደሚከበር ተነግሯል።
 
ግንባታው ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የከተማዋን ገጽታ በመገንባት ረገድም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
 
አሁን ላይ ስፍራው የመስቀል ደመራ በዓልን ማከበር በሚያስችል መልኩ ተዘጋጀቶ ማየታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጽእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናግረዋል።
 
በተመሳሳይ መስከረም 23 በአዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም፤ አባ ገዳዎች የማክበሪያ ስፍራ ተረክበዋል።
 
በቆንጂት ዘውዴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.