Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ ተምሳሌት ነው -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ከማዘጋጃ ቤት -የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት የምርቃት መርሐግብር ዝግጅት።
ከማዘጋጃ ቤት -የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት 3ነጥብ 5 ኪሎሜትር ርዝመት በ50 ስፋት የተሰራ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው።
በመርሐግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፣ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣የቀድሞ ምክትል ከንቲባ እና የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስትር ኢንጂነርር ታከለ ኡማ ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መአዛ አሸናፊ ፣የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ሚኒስትሮች ፣አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር÷የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ ተምሳሌት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ወይዘሮ አዳነች ፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ እያዘዙን ሳይሆን እያገዙን ጥቅላይ ሚኒስትሩ ለሰጡት አመራርና ክትትል ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ይህንን ስራ ያስጀመሩት ቀድሞ ን የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማም ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።
ምክትል ከንቲባዋ አያይዘውም ታሪክን የምናፈርስ ሳይሆን የምንገነባ በመሆን በቃጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
ይህ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትም1ሺህ 400 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎችን የሚያስቆሙ ባለሁለት የመሬት ውስጥ የግንባታ መሰረቶች ስማርት ፓርኪንግ ያለው ነው ብለዋል።
በተጨማሪም 35 ሱቆች፣ 140 መፀዳጃና 20 መታጠቢያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች የቢሮ መገልገያ ክፍሎች፣ 6 ዘመናዊ ሊፍቶች፣ ለ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ የደህንነት ካሜራዎች፣ ዘመናዊ ዲጂታል ስክሪኖች እና የእሳት መከላከያ ጭምር አለው፡፡
ከዚያም ባለፈ የቴሌኮም፤ባንክ ፤ሱቆች 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ አሉት፡፡
ሱቆቹ የኢትዮጵያን ባህል እና ቅርሶች የሚያሳዩ እና ለጎብኚዎች እንዲሸጡ በሚያመች ሁኔታ ተገንብተዋል፡፡
ቦታው ታሪካዊ ቅርስነቱን ጠብቆ ለደመራ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፣ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሆኖ ነው የተገነባው ብለዋል፡፡
ዛሬን አሻግረን እየተመለከትን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ንጹና ጽዱ እናደርጋታለንም ነው ያሉት።

ስኬት የብዙ አካላት ትብብርና ልፋት በመሆኑ በዚህ ፕሮጀክት ስራ ላይ የተሳተፉትን የቻይናውን ሲሲቲቪ ኩባንያ፣አማካሪውን እና ሁሉም አካትላት ማመስገን እወዳለሁ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+4
90,991
People Reached
8,900
Engagements
Boost Post
2.3K
66 Comments
102 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.